ከፓኪስታን እስከ መካ 4 ሺህ ኪሎ ሜትሮችን በእግሩ በመጓዝ የሐጅ ጉዞውን ያሳካው ወጣት

71

ባሕር ዳር: ሰኔ 21/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ፓኪስታናዊው ወጣት ለሃጅ ሃይማኖታዊ ጉዞ ጃንጥላ እና በጀርባ የሚታዘል ሻንጣ ይዞ 4 ሺህ ኪሎ ሜትር በእግሩ በመጓዝ ሳዑዲ አረቢያ መካ ደርሷል።

አቅሙ ያለው ሙስሊም በሕይወት ዘመኑ ቢያንስ አንድ ጊዜ ለማሳካት የሚመኘውን የሃጅ ጉዞ ኡስማን አርሻድ በእግሩ በመጓዝ አውን አድርጎታል።

ጉዞውን የጀመረው ከትውልድ ከተማው የፓኪስታኗ ኦካራ ሲሆን፣ ስድስት ወራትን ተጉዞ ነው መካ የደረሰው።

ቢቢሲ እንደዘገበው፣ ቅዱሱን የሃይማኖታዊ ጉዞ በእግሩ የፈጸመው ኡስማን ሺዎችን ኪሎ ሜትሮች በመጓዝ ሳዑዲ አረቢያ መካ ለመድረስ አራት ሀገራትን አቆራርጧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሳዑዲው ንጉሥ ሳልማን 5 ሺህ ለሚጠጉ ሐጃጆች የዒድ አል አድሃ አረፋ ወጪን ሸፈኑ፡፡
Next articleእስከ ቂያማ የምትዘልቀው የዘምዘም ውኃ