
ባሕር ዳር: ሰኔ 21/2015 ዓ.ም (አሚኮ) 1 ሺህ 444ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ በተገኙበት በጅግጅጋ ስታዲየም በድምቀት እየተከበረ ነው።
በዓሉ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች ነው እየተከበረ እንደሚገኝ ኢቢሲ ዘግቧል።
በአከባበር ስነ-ስርዓቱ ሰላት እና ተክቢራን ጨምሮ የተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች በመከናወን ላይ ናቸው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!