1ሺህ 444ኛው የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል በሐረሪ ክልል በኢማም አህመድ ስታድየም እየተከበረ ነው።

32

ባሕር ዳር: ሰኔ 21/2015 ዓ.ም (አሚኮ) 1ሺህ 444ኛው የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል በሐረሪ ክልል በኢማም አህመድ ስታድየም በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች በመከበር ላይ ይገኛል።

1ሺ 444ኛው የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል የሐረሪ ክልል ርዐሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፣ የእስልምና ሀይማኖት አባቶች እና የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት ነው በድምቀት በመከበር ላይ የሚገኘው።

በዓሉ በፀሎት ፣ በስግደት እና በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች እየተከበረ ይገኛል።

በበዓሉ አከባበር ስነ ስርዓት ላይ በዓሉ የእዝነት፣ የመረዳዳት እና የመተጋገዝ በመሆኑ ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር የተቸገሩትን በመርዳት የታሰሩትን በመጠየቅ አና በመደጋገፍ እንዲያከብር መልዕክት ተላልፏል።

ምዕመኑ ሃይማኖቱ በሚያዘው መሰረት በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች በዓሉን ሊያከብረው እንደሚገባም ተጠቁሟል።

በዓሉን እያከበሩ የሚገኙ ምዕመናን የሰላም እና የፍቅር ከተማ በሆነችው ሐረር በዓሉን በድምቀት እያከበሩ መሆኑን ገልፀው፣ በዓሉን በመረዳዳት እና በመተጋገዝ እንደሚያከብሩት ተናግረዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ኅብረተሰቡ የአረፋን በዓል ሲያከብር የመረዳዳት ባህሉን ይበልጥ በማጎልበት ሊኾን ይገባል” ርእሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሀሰን
Next articleየዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በጅግጅጋ ከተማ እየተከበረ ነው።