“ኅብረተሰቡ የአረፋን በዓል ሲያከብር የመረዳዳት ባህሉን ይበልጥ በማጎልበት ሊኾን ይገባል” ርእሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሀሰን

41

ባሕር ዳር: ሰኔ 21/2015 ዓ.ም (አሚኮ) 1 ሺህ 444ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል ዛሬ በአሶሳ ከተማ በሚገኘው አሕመድ ናስር መታሰቢያ ስታዲየም በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች በድምቀት ተከብሯል።

በበዓሉ አከባበር ላይ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች ተገኝተዋል።

በበዓሉ ላይ የተገኙት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሀሰን ኅብረተሰቡ የአረፋን በዓል ሲያከብር የመረዳዳት ባህሉን በማጠናከር ሊሆን ይገባል ብለዋል።

የእምነቱ ተከታዮች በዓሉን ሲያከብሩ በመደጋገፍ እና በመከባበር እንዲያሳልፉ ርእሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሀሰን ጥሪ አቅርበዋል።

ኢዜአ እንደዘገበው የክልሉ ማኅበረሰብ አንድነት እና ሰላም እየተጠናከረ መምጣቱን ገልጸው የክልሉ መንግስት የኅብረተሰቡን ጥያቄ ለመመለስ ጥረት እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል የሶላት ሥነ ሥርዓት በሠላም ተጠናቋል- የፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል
Next article1ሺህ 444ኛው የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል በሐረሪ ክልል በኢማም አህመድ ስታድየም እየተከበረ ነው።