
ባሕር ዳር: ሰኔ 21/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል የሶላት ሥነ-ሥርዓት በሠላም መጠናቀቁን የፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ።
የሶላት ሥነ-ሥርዓቱ በሠላም እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ኹሉ ግብረ ኃይሉ ምስጋና ማቅረቡን ከአዲስ አበባ ፖሊስ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡
1 ሺህ 444ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በአዲስ አበባ ስታዲየም በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ሀይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት መከበሩንም አስታውቋል፡፡
ሕዝበ ሙስሊሙ ሥነ ሥርዓቱ በሠላም እንዲጠናቀቅ ከመላው የከተማ ነዋሪዎችና የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን ላበረከተው አስተዋፅኦ የፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!