
ባሕር ዳር: ሰኔ 21/2015 ዓ.ም (አሚኮ) 1 ሺህ 444ኛው ዓመተ ሂጅራ የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል በመላው ሙስሊሞች ዘንድ እየተከበረ ነው፡፡
በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም እየተከበረ ያለው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሙስሊሞች ተሳትፊ ሆነዋል፡፡
በበዓሉ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል እስልምና ጉዳይ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሼህ ሙሐመድ አንዋር በዓሉ የደስታ ይሆን ዘንድ የአሏህን ትዕዛዛት ማክበርን እንዳትረሱ ብለዋል፡፡
“የደስታ ቀን ይሆን ዘንድ የተራበ ቤተሰብን እንዳትረሱ” ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ በተለያዩ ውስጣዊ ችግሮች ከሀገራቸው እና ከወገኖቻቸው ተለይተው በስደት የሚኖሩትን አስታውሱ ብለዋል፡፡ ከሶላት በኋላ በየቤታችን በሚኖረው የእርድ ሥርዓት ላይም ሃይማኖቱ በሚያዝዘው መልኩ ለተቸገሩ፣ ለቤተሰቦቻችን እና ለጓደኞቻችን ማካፈልን እንዳትረሱ ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!