“እንኳን ለዒድ አል አድሃ በዓል አደረሳችሁ!” ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)

49

ባሕር ዳር: ሰኔ 20/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) “እንኳን ለዒድ አል አድሃ በዓል አደረሳችሁ!” ብለዋል።

ሀገራችን የበርካታ ኃይማኖቶችና ባሕሎች ባለቤት ናት፡፡ እነዚህ ኃይማኖታዊና ባሕላዊ እሴቶቻችን የእኛነታችን መገለጫ፤ የአብሮነታችን ማሳያዎች ናቸው ብለዋል።

የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በዓለም መቻቻል፣ መከባበር፣ መረዳዳት፣ ተካፍሎ የመብላትና በማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ የሚያጋጥሙ ልዩነቶችን በጋራ የመፍታት እሴት ጎልቶ የሚታይበት በዓል ነው ብለዋል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)

ልዩነቶችን በጋራ የመፍታትና ሰላምን የማጽናት ኃላፊነት የሁሉም ኃይማኖት አባቶችና ተቋማት ቀዳሚ አስተምህሮ ነው። ይሁን እንጅ ዘላቂ ሰላም የሚጸናው በሁሉም ዜጎች የጋራ ጥረት በመሆኑም ሁላችንም ለሰላም መስፈን ባለቤቶች መሆን አለብን ነው ያሉት።

ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልእክት ሕዝበ ሙስሊሙም በዓሉን ሲያከብር ኃይማኖታዊ ሕግጋቱ በሚያዘው መሰረት ለሰላም ዘብ በመቆም፣ የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት፣ በመደጋገፍና በአንድነት ሊሆን ይገባል ብለዋል። ለእምነቱ ተከታዮች በሙሉ 1ሺ 444ኛው የዒድ አል አድሀ በዓል የሰላም፣ የመተሳሰብና የአንድነት እንዲሆን በራሴና በክልሉ መንግሥት ስም እመኛለሁ ብለዋል።

ኢድ-ሙባረክ!

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ታላቅ ታሪክ ያለበት፣ መልእክተኞች ያረፉበት”
Next article“አንድን ነገር ትጠሉት ይኾናል ያ ነገር በጎ ኾኖ ሳለ፣ አንድን ነገር ትወዱት ይኾናል ያ ነገር ለእናንተ መጥፎ ኾኖ ሳለ”