ግምታዊ ዋጋው ከ28 ሚሊዮን 386 ሺህ ብር በላይ የሚሆን አደንዛዥ ዕፅ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

140

ሕዳር 25/2012 ዓ.ም በጉምሩክ ኢንተለጀንስ ሠራተኞች እና በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች አማካኝነት በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የዓለም አቀፍ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል ነው አደንዛዥ ዕፁ የተያዘዉ፡፡

ዕፁን ሲያዘዋውሩ የተገኙትም የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ናቸው፡፡ ኖምዛሞ ግላዲየስ ቦዛ የተባለች ደቡብ አፍሪካዊት፣ መነሻዋ ከደቡብ አፍሪካ መዳረሻዋ ደግሞ ህንድ ደልሂ ሆኖ 7 ነጥብ 4 ኪግ እና አንቲቃ ሱለይማን ቂዚ አባሶባ የተባለች የአዘር ባጃን ዜጋ ከሞስኮ በአዲስ አበባ ወደ ባንኮክ ለመጓዝ ስትሞክር 4 ኪግ ኮኬይን ይዘው በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የገቢዎች ሚኒስቴር በማኅበራዊ ገጹ እንዳስታወቀው የተያዘው ኮኬይን ግምታዊ ዋጋው ከ28 ሚሊዮን 386 ሺህ ብር በላይ ነው፡፡

ሕገ ወጥነት በሌሎች አገሮች ዜጎች በኢትዮጵያ አየር መንገድና በኢትዮጵያ በኩል እየተፈጸመ በመሆኑ ኅብረተሰቡ ከሕገ ወጥ ድርጊት እራሱን በመቆጠብ ድርጊቱ ሲፈፀምም በመጠቆምና በመከላከሉ እንዲሳተፍ ጥሪ ቀርቧል፡፡

Previous articleከተሞች ተቋማዊ አሠራራቸውን በማሻሻል የመልማት አቅማቸውን ማጠናከር እንደሚገባቸው ተመላከተ።
Next articleበ451 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ መርሀ ግብር ይፋ ተደረገ፡፡