የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ.ር )ከፈረንሳይ ንግድ ምክር ቤት አባላት ጋር ተወያዩ።

23

ባሕር ዳር: ሰኔ 20/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ.ር) ከፈረንሳይ ንግድ ምክር ቤት አባላት ጋር ተወያይተዋል፡፡

ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር ) ለልዑካን ቡድኑ አባላት ስለ ምዕራፍ ሁለት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ይዘትና ዝግጅት አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በተለይም መንግሥት የግሉን ዘርፍ የኢኮኖሚ ተሳትፎ ለማሳደግ በማሻሻያው ያስቀመጣቸውን ቁልፍ ሃሳቦች አስረድተዋል፡፡

የፈረንሳይ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት የኢንቨስትመንት ተሳትፎም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የፈረንሳይ ንግድ ምክር ቤት ልዑካን ቡድን አባላት በበኩላቸው በርካታ የፈረንሳይ ባለሃብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች እየተሳተፉ እንደሚገኙ አንስተዋል፡፡

በቀጣይም ያላቸውን ተሳትፎ ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላቸው ማረጋገጣቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ኡድሂያ-የአሏህ የበረከት መንገድ”
Next articleትምህርት ሚኒስቴር በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን 45 ትምህርት ቤቶች በክልሉ እያስገነባ መኾኑ ተገለጸ፡፡