“በፈረንጆቹ 2030 የንጹህ መጠጥ ውኃ አቅርቦትን ለሁሉም ለማዳረስ እየተሠራ ነው” የውኃ እና ኢነርጅ ሚኒስቴር

65

አዲስ አበባ: ሰኔ 19/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የዉኃ እና ኢነርጅ ሚኒስቴር 11ኛውን የዉኃ ሀብት አሥተዳደር ጉባዔ እያካሄደ ይገኛል። በዚህ ጉባዔ በዉኃ ሀብት እና አጠቃቀም ላይ የሚሠሩ አጋር አካላት እየተሳተፉ ነው።

የዉኃ እና ኢነርጅ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ.ር) ባለፉት ዓመታት የመጠጥ ዉኃን ለዜጎች ማዳረስ እና ሳኒቴሽን ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ነዉ ብለዋል። ያለዉን የዉኃ ሀብት በአግባቡ መንከባከብና ከሰዎች ንክኪ ነጻ ማድረግም ትኩረት ተሰጥቶታልም ነዉ ያሉት።

ጉባዔዉ ይህንን ዘርፍ ለማዘመን እንደሚያስችልም አስረድተዋል፡፡ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በቀጣይ ዓመታት የዉኃ ሀብትን ለማዘመን የያዘቻቸዉን ግቦች አንስተዋል። በ2030 የንጹህ መጠጥ ውኃን መቶ በመቶ ለማኅበረሰቡ ማዳረስ፣ ታዳሽ ኀይልን ማመንጨት፣ የዉኃ ሀብት አሥተዳደርን ማዘመን እና ያለዉን የከርሰ ምድር ዉኃ ማጥናት ላይ ትኩት ተሰጥቶ ይሠራልም ብለዋል።

ከዉኃ ሀብት ጋር ተያይዞ ሳኒቴሸን ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መኾኑን የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ.ር) ተናግረዋል፡፡ በተለይም ያለዉን የዉኃ አጠቃቀም ማዘመን እና የመጸዳጃ ቤት ሽፋንን ማሳደግ በዋናነት ትኩረት የተሰጠዉ ነዉ ብለዋል።ይህ ፎረም ደግሞ በግሉ ዘርፍ የሚገኙ ተቋማትን ያካተተ መኾኑ ለዉጦች እንዲመጡ አስፈላጊ ነዉ ብለዋል የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ።

ከንጹህ መጠጥ እና ከንጽህና አጠባበቅ ጋር ተያይዞ ከጤና ኤክስቴሽን ጀምሮ እየተሠራ ስለመኾኑም ተገልጿል።

ዘጋቢ፡- ኤልሳ ጉኡሽ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ምዕመናን ለሐጂ ሳዑዲ አረቢያ ገብተዋል፡፡
Next articleብሩህ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ውድድር የሽልማት ሥነ ሥርዓት በመካሄድ ላይ ይገኛል።