
ወልድያ: ሰኔ 18/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ውድድሩ ከሰኔ18 እስከ ሀምሌ 06/2015 የሚቆይ ሲሆን 37 ክለቦች ይሳተፋሉ።
ውድድሩን ከ1 አስከ 8 ኾነው የሚያጠናቅቁ ክለቦች ወደ አንደኛ የአማራ ሊግ እንደሚያድጉም ተገልጿል፡፡
በውድድሩ የተገኙት የአማራ ክልል ወጣትና ስፖርት ቢሮ ኀላፊ እርዚቅ ኢሳ ውድድሩ የክልሉን ስፖርት ለማሳደግና ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ያግዛል ብለዋል፡፡
የወልድያ ከተማ ከንቲባ ዱባሌ አብራሪ ውድድሩ ለከተማዋ ኢኮኖሚና ስፖርት መነቃቃት ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል።
ስፖርታዊ ውድድሩ ወንድማማችነትን እና አብሮነትን ያጠናክራል ያሉት አቶ ዱባለ የከተማው ማኀበረሰብ ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ የስፖርት ተሳታፊዎችን ለመቀብል ሰፊ ዝግጅት ሲያደረግ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ:-ባለ ዓለምየ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!