
ባሕር ዳር: ሰኔ 18/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ያደረጉት ጨዋታ በአንድ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው የ28ኛ ሳምንት መርሐ ግብር 9 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ቡና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫውተዋል፡፡
በተጠባቂው ደርቢ ጨዋታም ኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
ለቅዱስ ጊዮርጊስን እስማኤል ኦሮ አጎሮ 66ኛው ደቂቃ ላይ ግቧን ሲያስቆጥር ለኢትዮጵያ ቡና ደግሞ ብሩክ በየነ በ72ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ አሳርፏል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!