ከተሞች ተቋማዊ አሠራራቸውን በማሻሻል የመልማት አቅማቸውን ማጠናከር እንደሚገባቸው ተመላከተ።

190

የኢፌዴሪ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በዓለም ባንክ ድጋፍ ተጠቃሚ ከተሞች ተቋማዊ መሠረተ ልማት እንቅስቀሴ ዙሪያ እየመከረ ነው። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የ2012 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ከክልልና ከፌደራል ተንቀሳቃሽ ባለሙያዎች ጋር ነው እየመከረ የሚገኘው።

በውይይቱ በኢትዮጵያ ከተሞች የሚገኙ ባለድርሻዎች እየተሳተፉ ነው፤ ፕሮግራሙ ጠንካራና ደካማ አፈፃፀሞችን የሚገመግሙ ይሆናል።

የዓለም ባንክ የከተሞች ተቋማዊና መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ባሉ 117 ከተሞች ነው ተግባራዊ እየሆነ የሚገኘው። ፕሮግራሙ በ2001ዓ.ም በ19 ከተሞች የጀመረ ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ አድማሱን እያሰፋ እንደሚገኝ በኢፌድሪ ከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የፕሮግራሙ አስተባባሪ አቶ አለመሰየሁ አሊቶ ለአብመድ ተናግረዋል።

Previous articleበእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ 15ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ማንቸስተር ዩናይትድ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል፡፡
Next articleግምታዊ ዋጋው ከ28 ሚሊዮን 386 ሺህ ብር በላይ የሚሆን አደንዛዥ ዕፅ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡