
ባሕር ዳር: ሰኔ 18/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ሹመት ሰጥተዋል። ርአሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መሥተዳድር የሕዝብ ግንኙነትና የአደረጃጀት ዘርፍ አማካሪ ሹመት የሰጡ ሲሆን አቶ ይርጋ ሲሳይን ከሰኔ 17/2015 ዓ.ም ጀምሮ የዘርፉ ኃላፊ አድርገው ሹመዋል።
ርእሰ መሥተዳድሩ የሕዝብ ግንኙነትና የአደረጃጀት ዘርፍ አማካሪ አድርገው የሾሟቸው አቶ ይርጋ ሲሳይ በተለያዩ የሕዝብ፣ የመንግሥትና የፓርቲ አደረጃጀቶች የረዥም ጊዜ ልምድ ያላቸው መሆኑ ታውቋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
