“ሙስናና ብልሹ አሠራር ሀገርን በእጅጉ እየጎዳ በመኾኑ ታግሎ ማስተካከል ከወቅቱ አመራር የሚጠበቅ ነው” የደቡብ ጎንደር ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት

52

ደብረ ታቦር : ሰኔ 18/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ጎንደር ዞን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ለከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ”መፍጠርና መፍጠን” በሚል በተዘጋጀ ሠነድ ላይ ስልጠና መሥጠት ጀምሯል።

ለሦስት ቀናት በሚቆየው የስልጠና መክፈቻ ላይ የዞኑ ብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ጥላሁን ደጀኔ የስልጠናው ዓላማ አመራሩ በሀገር ጉዳይ ላይ ተወያይቶ፤ በወል እውነታ ላይ ተግባብቶና የአመራር አንድነት ይዞ እንዲወጣ ለማስቻል መኾኑን ተናግረዋል። አመራሩ አንድ ሐሳብ እንዲይዝና ሀገራዊ ወንድማማችነትንና አቅምን ጨምሮ ሕዝብ እንዲመራ እንዲሁም ሀገር በማልማት ድህነትን ለማስወገድ እንደሚያስችለውም አስረድተዋል።

የብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ይርጋ ሲሳይ ባስተላለፉት መልዕክት ሙስናና ብልሹ አሠራር ሀገርን በእጅጉ እየጎዳ በመኾኑ ታግሎ ማስተካከል ከወቅቱ አመራር የሚጠበቅ መኾኑን አስገንዝበዋል።

የከረረና ጫፍ የረገጠ ሃሳብ ለሀገር ስለማይጠቅም ምክክርና ውይይትን ማስቀደም ይገባል ያሉት አቶ ይርጋ ከዚህ በፊት ከነበረው የአመራርና የልማት ጉዞ በመሻሻል ስኬትን በማፅናትና ችግሮችን በማስወገድ መፍጠርና መፍጠን አስፈላጊ መኾኑን አሳስበዋል።

በስልጠናው የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የምሁራን አደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ደግሰው መለሰን ጨምሮ የደቡብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ አመራሮችና በዞኑ የሚገኙ የገጠርና ከተማ የወረዳ አመራሮች እየተሳተፉ ነው።

ዘጋቢ፦ ዋሴ ባየ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“29 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ተዘዋዋሪ ብድር ለሸማች ማኅበራት በማቅረብ እያጋጠመ ያለውን የዋጋ ንረት ለመከላከል እየሠራሁ ነው” የምዕራብ ጎጃም ዞን
Next articleከ19 ሺህ በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርገው የእግረኛ ተንጠልጣይ ድልድይ ለአገልግሎት ክፍት ኾነ።