የጂቡቲ መንግስት የሀገሪቱን የፖሊስ የክብር ኒሻን ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ሸለመ ።

76

ባሕር ዳር: ሰኔ 17/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የጂቡቲ መንግስት የሀገሪቱን የፖሊስ የክብር ኒሻን ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ሸለመ።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል፤ የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ኅብረት ድርጅት ፕሬዚዳንት ከጅቡቲ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልቃድር ካሚል መሀመድ የፖሊስ የክብር ኒሻኑን ተቀብለዋል።

46ኛ ዓመት የጅቡቲ ብሔራዊ ፖሊስ የምስረታ በዓል ቀን መከበሩንም የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

ኮሚሽነር ጀነራል ለሽልማቱ የበቁት የኢትዮ-ጂቡቲ ድንበር ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ በተለይም ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ በመከላከል ውጤት በመገኘቱ ነው ተብሏል፡፡

እንዲሁም በሁለቱ ሀገራት መካከል እየተፈጠረ ያለውን ግንኙነትና ትብብር በማጠናከር በቀጣናው ከፍተኛ ለውጥ እንዲመጣ ላበረከቱት አስተዋፆ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ፤ በጅቡቲ ብሔራዊ ፖሊስ የተሰጠው የፖሊስ የክብር ኒሻን ለእርሳቸው ብቻ ሳይሆን ለተቋሙ የተሰጠ ሽልማት መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየመቄት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ከ300 በላይ በተለያዩ ሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ፡፡
Next articleዓለማቀፍ የምግብ ድጋፍ የተቋረጠበትን ምክንያት ለይቶ ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ከረጅ ድርጅቶች ጋር የጋራ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየሠራ መኾኑን የኢትዮጵያ መንግስት አስታወቀ።