ከ232 ሺህ በላይ ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ወደ አማራ ክልል መላኩን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ።

53

አዲስ አበባ: ሰኔ 17/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የማዳበሪያ እጥረትን ለመፍታት መንግሥት ወደ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ ግዥ መካሄዱን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ገልጿል።

የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት በግብርናዉ ዘርፍ የተሠሩ ሥራዎች ላይ በዛሬ መግለጫው ማብራሪያ ሰጥቷል።

የመንግሥት ኮምዩንኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ እንዳሉት በበልግ እርሻ ከ2 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ሄክታር በዘር ተሸፍኗል ብለዋል።

በተጨማሪ በመኸር እርሻ ወደ 11 ሚሊዮን መሬት መታረሱንም ገልጸዋል። ወደ 2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሔክታሩ በዘር ተሸፍኗል ብለዋል።

በክላስተር ወደ 4 ነጥብ 2 ሚሊዮን መሬት መታረሱን ገልጸው፤ ከዚህ ዉስጥ ደግሞ 1 ነጥብ 5 በዘር ተሸፍኗልም ሲሉ አንስተዋል። የአፈር ማዳበሪያ እጥረትን ለመፍታት የተሠሩ ሥራዎችን ያነሱት ሚኒስትር ዴኤታዋ ወደ 1 ነጥብ 5 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ግዥ ተፈጽሟልም ብለዋል።

ከዚህ ውስጥ 232 ሺህ በላይ ሜትሪክ ቶን ወደ አማራ ክልል ተልኳልም ብለዋል።

ዘጋቢ፦ ኤልሳ ጉዑሽ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleዓለም አቀፍ ተቋማት ቃል የሚገቡትን ወደ ተግባር እንዲቀይሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መጠየቃቸውን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ።
Next article“ኢትዮጵያ ያላትን ትክክለኛና ድንቅ ማንነቷን በአግባቡ ለማስተዋወቅ የሚያስችላት የቱሪዝም አውደ ርእይ ታካሂዳለች” የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት