
ባሕር ዳር: ሰኔ 17/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በፓሪስ ላደረጉላቸው አቀባበል እና ሽኝት ምስጋና አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት “የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮንን በፓሪስ ላደረጉልን አቀባበል እና ሽኝት ምስጋናዬን አቀርባለሁ”ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም “ፍሬያማ ለነበረው አዲስ የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስምምነት ጉባዔ እንዲሁም የአፍሪካ ሀገሮችን ለመደገፍ ላሳዩት ፈቃደኛነትም አመሰግናቸዋለሁ” ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!