
ባሕር ዳር: ሰኔ 17/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለማስጀመር ሐዋሳ ገብተዋል።
ፕሬዝዳንቷ፣ በሁለተኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የውሃማ አካላትን ከብክለት ለመጠበቅ የሚከናወን ችግኝ ተከላ በሐዋሳ ሐይቅ ዳርቻ የሚያስጀምሩ ሲሆን ሌሎች የልማት ሥራዎችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ኢቢሲ እንደዘገበው፤ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ሐዋሳ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!