ክልላዊ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ከፍተኛ የክልል እና የፌደራል የሥራ ኅላፊዎች በተገኙበት በደቡብ ጎንደር ዞን እየተካሄደ ነው።

48

ባሕር ዳር: ሰኔ 16/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የ2015 ዓ.ም የሁለተኛው ምዕራፍ የመጀመሪያው ዙር ክልላዊ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ ጎሃ ቀበሌ እያካሄደ ነው።

በመርሐ ግብሩ ላይ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፣ ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) እና ሌሎችም የፌደራል እና የክልል የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

በክልሉ በ2015 ዓ.ም በአምስተኛው አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል ታቅዶ እየተሠራ ነው። ከዚህ ውስጥ ከአንድ ቢሊዮን በላይ የሚኾነው ችግኝ በፕላስቲክ ቱቦ የተፈላ ነው። በሥራው ላይ 3 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሕዝብ ተሳታፊ እንደሚኾንም ተገልጿል።

ዘጋቢ፡- አሜናዳብ አራጋው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“170 ሺህ የሚጠጉ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን ይወስዳሉ” ትምህርት ሚኒስቴር
Next articleበስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ በ2014 ዓ.ም ከተተከሉ ችግኞች 88 በመቶውን ማጽደቅ እንደተቻለ የፓርኩ ጽሕፈት ቤት ገለጸ።