
ባሕር ዳር: ሰኔ 15/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ብርሃን ከተማ የተገነባው የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ሚኒ ባስ መኪኖችን መገጣጠም መጀመሩን አስታውቋል።
ፋብሪካው በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ሚኒባስ፣ መለስተኛ አውቶቡስ እና የከተማ አውቶቡስ ተሽከርካሪዎችን የማምረት አቅም አለው።
ፋብሪካው በመጀመሪያ ዙር 216 በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ሚኒ ባስ መኪኖችን ከደብረ ብርሃን በተጨማሪ ገላን በሚገኘው መገጣጠሚያው መገጣጠም መጀመሩን ከበላይነህ ክንዴ ግሩፕ የተገኘው መረጃ ያመላክታል። በደብረ ብርሃን ከተማ በተገነባው ፋብሪካ በአሁኑ ሠዓት ከ250 በላይ ለሚደርሱ ወገኖች የሥራ እድል መፍጠር ተችሏል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!