
ባሕር ዳር: ሰኔ 15/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ከልዑክ ቡድናቸው ጋር በፈረንሳይ ፓሪስ በአዲስ የዓለም አቀፍ ፋይናንስ ስምምነት ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ነው።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ባወጣው መረጃ “ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ከልዑክ ቡድናቸው ጋር ፈረንሳይ ፓሪስ በአዲስ የዓለም አቀፍ ፋይናንስ ስምምነት ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ነው” ብሏል።
በጉባዔው ላይ የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፣ የሳዑዲ ዓረቢያ ልዑል አልጋወራሽ ሙሐመድ ቢን ሰልማንን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች ተገኝተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!