በአፍሪካ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን በፍትሐዊነት መጠቀም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት እየተካሄደ ነው።

80

ባሕር ዳር: ሰኔ 15/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በአፍሪካ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን በፍትሐዊነት መጠቀም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

ውይይቱ እየተካሄደ ያለው “የእኩል ምክንያታዊ የድንበር ተፋሰስ ወንዞች ተጠቃሚነት ለአፍሪካ ብልጽግና ወሳኝ ነው “በሚል መሪ ሀሳብ ነው።

በመድረኩ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እንዲሁም ከናይል ተፋሰስ ሀገራት እና የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ተገኝተዋል።

መድረኩ ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን ዓላማውም የድንበር ተሻጋሪ ውኃዎችን ምክንያታዊ እና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ የመጠቀም ጉዳይን እውን ማድረግ በሚቻልበት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተመላክቷል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ወደ ፍርድ ቤት ከቀረቡ ጉዳዮች ከ29 ሺህ በላይ መዝገቦችን በእርቅ መፍታት ተችሏል” የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
Next articleጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በፓሪስ በአዲስ የዓለም አቀፍ ፋይናንስ ስምምነት ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ነው