በ12 ክለቦች መካከል ሲካሄድ የቆየው የአማራ ሊግ ቮሊቦል ውድድር በባንጃ ክለብ አሸናፊነት ተጠናቀቀ።

56

ባሕር ዳር: ሰኔ 14/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ቮሊቦል ፌዴሬሽን አዘጋጅነት በባሕር ዳር ላለፋት ሁለት ሳምንታት በ12 ክለቦች መካከል ሲካሄድ የቆየው የአማራ ሊግ የቮሊቦል ውድድር በባንጃ ክለብ አሸናፊነት ተጠናቋል።

ለፍጻሜ በደረሱት ባንጆ እና ወሎ መቅደላ ክለቦች መካከል የፍጻሜ ጨዋታ ተካሂዶ ባንጃ 3 ለ 2 በኾነ ውጤት መቅደላን በማሽነፍ የ2015 ዓ.ም የአማራ ሊግ ቮሊቮል ውድድር ሻምፒዮና ሆኗል። ድንቅ ፉክክር ያደረገው የወሎ መቅደላ ቮሊቦል ክለብ ሁለተኛ ኾኖ ሲያጠናቅቅ የዳንግላ ወረዳ ደግሞ ሦስተኛ ደረጃን ይዟል።

የ2015 ዓ.ም የአማራ ሊግ ቮሊቦል ውድድር የስፖርታዊ ጨዋነት አሸናፊ እና ተሸላሚ ደግሞ የወሎ መቅደላ ቮሊቦል ክልብ ኾኖ ተመርጧል።

በውድድሩ ፍጻሜ ላይ የተገኙት የእለቱ የክብር እንግዳ የአማራ ክልል የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኅላፊ አቶ ተፈሪ ካሳ ለአሸናፊ ክለቦች ዋንጫ እና ሜዳሊያ አበርክተዋል።

ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሕዝቡ የሚያነሳቸውን ቅሬታዎች መፍታት የሁሉም ተቋማት ዋነኛ ተግባር ሊሆን ይገባል” የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት
Next article“ለአምስት የውጭ ሀገር ባንኮች ፈቃድ ሊሰጥ ነው” የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ