
ባሕር ዳር: ሰኔ 14/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን 200 ጊዜ ተሰልፎ በመጫዎት ስሙ በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ሰፍሯል፡፡
ሮናልዶ ትላንት ምሽት በአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ሀገሩ ፖርቹጋል አይስላንድን በገጠመችበት ጨዋታ 200ኛ ጨዋታውን ለብሕራዊ ቡድኑ አድርጓል፡፡
በጨዋታውም ግብ አስቆጠሮ ሀገሩን አሸናፊ ማድረግ መቻሉ ነው የተገለጸው፡፡
ይህን ተከትሎም ሮናልዶ በወንዶች ምድብ ለብሔራዊ ቡድን ብዙ ጊዜ የተሰለፈ ተጫዋች በመሆን የዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ሰርተፍኬትን ከጨዋታው በኋላ ተቀብሏል፡፡
ሮኖልዶ ሰርተፍኬቱን ከተቀበለ በኋላ “እዚህ እደርሳለሁ ብየ አላስብኩም፣ይህ ትልቅ ክብር ነው፣አዳዲስ ታሪኮችን ማስመዝገቤን እቀጥላለሁ” ብሏል፡፡
ቀደም ሲል ክብረ ወሰኑ በኩዌቱ አጥቂ ባድር አል ሙታዋ ተይዞ የነበረ ሲሆን፥፤ ሙታዋ ለኩዌት ብሔራዊ ቡድን 196 ጊዜ ተሰልፎ ተጫውቷል፡፡
የ38 ዓመቱ አጥቂ ክርስቲያኖ የፖርቹጋል ብሄራዊ ቡድን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሲሆን÷ 200 ጊዜ ተሰልፎ 123 ግቦችን እንዳስቆጠረ ሜይል ስፖርት ዘግቧል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!