
ወልድያ: ሰኔ 14/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የራያ አላማጣ ወረዳ፣ የአላማጣ ከተማና የራያ ባላ ሕዝብ ዛሬም የማንነት ጥያቄዎችን ይዞ አደባባይ ወጥቷል።
የማንነት ጥያቄያችን አፋጣኝ ምላሽ ይሰጠው፤ እኛ አማራ ነን የምንለው ከጥንትም አማራ ስለኾንን እንጂ ዛሬ አማራ እንሁን አላልንም ሲሉ ድምፃቸውን አሰምተዋል።
የፌዴራል መንግሥትም በአፋጣኝ መልስ እንዲሰጣቸው በአደባባይ ጠይቀዋል።
የራያን ሕዝብ በጀት አማራ ክልል ኘሮጀክት እያጠፈ እየሸፈነ እንደሚገኝ የገለጹት የአደባባይ ሰልፈኞቹ የራያ ሕዝብ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ የፌዴራል መንግሥት በጀቱ ሊለቀቅለት ይገባል ነው ያሉት።
የቴሌ፣ የኤሌክትሪክ ኀይልና ሌሎች የፌዴራል ተቋማት በራያ አገልግሎታቸውን ሙሉ በሙሉ እንዲጀምሩና የኢትዮጵያ የልማት ተካፋይ ይሁኑ ሲሉ ጠይቀዋል።
“በተደጋጋሚ ሰልፍ እየወጣን ለምጠይቃቸው ጥያቄዎች በፌደራል መንግሥት በኩል ምላሹ መዘግየቱ ቅሬታን ፈጥሮብናል” ብለዋል ሰልፈኞቹ ባስተላለፉት መልእክት።
ዘጋቢ፦ካሳሁን ኃይለሚካኤል
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!