የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች መንግስት የማንነት ጥያቄቸውን ሕጋዊ እንዲያደርግላቸው በሰላማዊ ሰልፍ እየጠየቁ ነው።

82

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን የአለማጣ ከተማ ነዋሪዎች የአማራ ማንነት ጥያቄቸውን መንግስት በሕግ እንዲያረጋግጥላቸው በሰላማዊ ሰልፍ እየጠየቁ ነው።

የከተማዋ ነዋሪዎች በሰላማዊ ሰልፉ ፦

👉አማራ ነን እንጂ አማራ እንሁን አላልንም፣

👉 የፌደራል መንግስት ተቋማት ዲስትሪክት ወደ ሰሜን ወሎ ዞን ይዛወሩልንና ሌሎች የተለያዩ መፈክሮችን አሰምተዋል።

ሳይፈልጉ በኀይል አካባቢያቸው ወደ ትግራይ ተካሎ በነበረበት ሰላሳ ዓመታት የሰው ልጅ ሊፈፅመው የማይችል ሰብዓዊነት የጎደለው ግፍ ሲፈጽምባቸው እንደነበር ገልፀው፤ አሁን ላይ ግን በነፃነት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ተናግረዋል።

የማንነት ጥያቄያቸው ሕጋዊ ሆኖ እንዲረጋገጥላቸው በሰላማዊ ሰልፉ መጠየቃቸውን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

Previous articleርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ከአውሮፓ ኅብረት ተወካይ እና ከፈረንሳይ አምባሳደር ጋር ተወያዩ።
Next article“ደም በመለገስ በደም መፍሰስ ሕይወታቸውን የሚያጡ ወገኖችን መታደግ ይገባል” የኢትዮጵያ ደምና ሕብረ-ህዋስ ባንክ አገልግሎት