አሠልጣኝ ውበቱ አባተ የፋሲል ከነማ አሰልጣኝ ለመኾን ተስማማ

73

ባሕር ዳር: ሰኔ 12/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የቀድሞ የዋሊያዎቹ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በቀጣዩ ዓመት ፋሲል ከነማን ለማሠልጠን ስምምነት ላይ ደርሷል፡፡

የሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ መኾን የቻለው ፋሲል ከነማ 2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑ ይታወሳል፡፡

ክለቡ በዘንድሮው የውድድር ዓመት በ38 ነጥቦች 6ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

ወደ ቀድሞ አቋማቸው ለመመለስ ሁነኛ አሰልጣኝ ሲያፈላልጉ የቆዩት አፄዎቹ ከአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር አብሮ ለመሥራት ከስምምነት መድረሳቸውን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡

የስምምነቱ አጠቃላይ ዝርዝር ሁኔታዎች እና ይፋዊ የፊርማ ሥነ-ስርዓትም በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ ተጠቁሟል፡፡

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ቀደም ሲል በፋሲል ከነማ ውጤታማ ጊዜ ማሳለፋቸው የሚታወስ ነው፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበክልሉ ስምንት ዞኖች የወባ የሕሙማን ቁጥር እየጨመረ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡
Next articleከሥራ አጥ ቆጠራ የተሻገረ የሥራ እድል ፈጠራ ተግባር ያስፈልጋል!