
አዲስ አበባ: ሰኔ 12/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የግብርናዉን ዘርፍ ለማዛመን አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በፋይናንስ መደገፍ እንዳለባቸው የግብርና ሚኒስቴር ግርማ አመቴ ተናገሩ።
የግብርናዉን ዘርፍ ለማዘመን ያለመ ዉይይት ተካሂዷል።
በ10 ዓመት የግብርና መሪ እቅድ ዉስጥ የግብርናዉን ዘርፍ በፋይናንስ ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ ይሠራል ብለዋል የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ። ለአርሶ አደሩ እና አርብቶ አደሩ ብድር እንዲያገኝ ቢመቻችም አነስተኛ እና መካከለኛ አርሶ አደሮች የሚያገኙት ድጋፍ አናሳ መኾኑን ነው ያነሱት።
ይህ እቅድ ለበርካታ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በግብርና ዘርፍ ተጠቃሚ እንዲኾኑ የሚያስችል ነዉም ብለዋል።
የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ ሰለሞን ደስታ በግብርናዉ ዘርፍ ለተሰማሩ የሚቀርበዉ የፋይናንስ ድጋፍ አነስተኛ እንደነበር አንስተዉ አሁን ትኩረት ሰጥተን እየሠራን ነዉ ብለዋል።
የግብርናዉ ዘርፍ የውጭ ምንዛሬ ለማምጣት ያለዉ ድርሻ ከፍተኛ ነዉ፤ ዘርፉን በፋይናንስ መደገፍ ያስፈልጋል፤ ብሔራዊ ባንክም በዚህ ላይ ትኩረት አድርጎ ይሠራልም ነዉ ያሉት።
በግሽርናዉ ዘርፍ ለኅብረት ሥራ ማኅበራት እና ለኢንተርፕራይዞች 5 በመቶ የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲኾኑ እንደሚደረግ ተናግረዋል።
ዘጋቢ:- ኤልሳ ጉኡሽ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!