“ጅቡቲ ወደብ የደረሰው ከ7 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ እየተጓጓዘ ነው” ግብርና ሚኒስቴር

85

ባሕር ዳር: ሰኔ 12/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው በ2015/16 ምርት ዘመን የሚውል 12 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኮንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዥ ተፈጽሞ ወደ ሀገር ውስጥ የማጓጓዝ ሥራ እየተሠራ መሆኑን ገልጿል፡፡

እስከ ሰኔ 10/2015 ዓ.ም ድረስ ከ7 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ የደረሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 6 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኩንታል ወደ ሀገር ውስጥ ገብቶ እየተጓጓዘ ነው ብሏል፡፡

የማጓጓዝ ሥራው በመኪና እና በባቡር በፍጥነት እየተከናወነ ነው፤ አዳማ ካለው ባቡር ጣቢያ እንደደረሰ ወደ ኦሮሚያ፣ አማራና የሲዳማ ክልሎች እንደሚሰራጭ የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
በቀጣይም ለምርት ዘመኑ የሚያስፈልገውን የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶና አርብቶ አደሩ ለማቅረብ ሚኒስቴር በትኩረት እንደሚሠራም አስታውቋል፡፡

በክልሎች ያሉ የተለያዩ የኅብረት ሥራ ማኅበራት የማጓጓዝ ሥራውን በትኩረት እየሠሩ መሆኑንም ከግብር ሚኒስቴር ማህበራዊ ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየመንግሥታት ግንኙነት አዋጅ መመሪያ ላይ የሚመክር ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ውይይት እየተካሔደ ነው።
Next article“ሕገ ወጥነት የማዕድን ዘርፉ አንዱ ማነቆ ነው” የአማራ ክልል ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ