የመንግሥታት ግንኙነት አዋጅ መመሪያ ላይ የሚመክር ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ውይይት እየተካሔደ ነው።

73

አዲስ አበባ: ሰኔ 12/2015 ዓ.ም (አሚኮ) መድረኩ የክልል እና የፌዴራል መንግሥታት የሚኖራቸው ግንኙነት፤ አንድ ክልል የሚያወጣው ሕግ በሌላኛው ክልል ላይ ጫና እንዳያመጣ ለማድረግ ሃሳብ ያለው ነው።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ ላይ የክልል ርእሳነ መሥተዳድሮች፣ ከንቲባዎች እና የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚ ዘርፍ ሚኒስትሮች ተገኝተዋል።

የፌዴሬሽን ምክርቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በመንግሥታት በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 64 ንኡስ አንቀፅ 6 እና 4 እንዲሁም በአዋጅ 1231/2013 መሰረት የፌዴሬሽን ምክርቤት በክልሎች መካከል የሚነሱ አለመግባባቶችን ለመፍታት መፍትሔ ይሰጣል ይላል። ይህ መድረክ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በተሰጠው ሥልጣን መሰረት በጀት በሚገባው መንገድ እየተመደበላቸው እና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ክልሎቹ እያደጉ ስለመሆናቸው የፌዴሬሽን ምክርቤት ያረጋግጣል ይህ መድረክ የሱ አጋዥ ነው ብለዋል።

እንደ አፈ ጉባኤው ገለጻ ይህ መድረክ ወደፊት በክልሎች እና በክልሎች እንዲሁም በፌዴራል መንግሥት መካከል በፌዴሬሽን ምክርቤት አማካኝነት ሊኖር ስለሚገባ ቋሚ ጉባኤ ውሳኔ ያሳልፋል ብለዋል።

በምክር ቤቱ የመንግሥታት ግንኙነት የዲሞክራሲያዊ አንድነትና የሕገ መንግሥት አስተምህሮ ቋሚ ኮሚቴ ጸሐፊ በንቺ ይርጋ መለሰ እንዳሉት የፌዴሬሽን ምክር ቤት መድረኩ በክልሎች መካከል የተፈጠሩ ችግሮች ካሉ ይመለከታቸዋል።

ችግሮች በማየት ችግሮችን ለመፍታት ይጥራል። የፌዴራል ሥርዓቱም ኾነ ሕጋዊ የአሠራር እና መንገድ እንዲጎለብቱ ለማድረግ የመንግሥታት ግንኙነት ለመወሰን የወጣው አዋጅ 1231/2013 ወጥቶ ሥራ ላይ ይገኛል። ይህ አዋጅ በአንቀፅ 6 ባስቀመጠው መመሪያ መቅረፅ እንደሚያስፈልግ በማመላከቱ መመሪያ ለማውጣት የምክከር መድረክ ማዘጋጀት በማስፈለጉ ይህ መድረክ በመመሪያዎው ላይ አስፈላጊ ውሳኔዎችን ለማስቀመጥ የሚጠቅም መድረክ ነው ብለዋል።

እንደ ቋሚ ኮሚቴ ጸሐፊዋ ማብራሪያ አንድ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ለመፍጠር የፌዴራል ሥርዓት ማጠናከር ያስፈልጋል። ከመንግሥታት ግንኙነት አንዱ በክልል ርእሳነ መሥተዳድሮች፣ በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባዎች እና የሚመለከታቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን ያካተተ ነው በሚለው የበጀት መንግሥታት አዋጅ መሰረት የተቀመጠ በመኑ በመመሪያው ላይ ውይይት የሚያደርግ መድረክ ነው ብለዋል።

ዘጋቢ:- አንዱዓለም መናን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበኩር ጋዜጣ ሰኔ 12/2015 ዓ.ም
Next article“ጅቡቲ ወደብ የደረሰው ከ7 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ እየተጓጓዘ ነው” ግብርና ሚኒስቴር