
ደባርቅ: ሰኔ 11/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን የምዕራብ ጠለምት ወረዳና የማይጠብሪ ከተማ ነዋሪዎች በሰላማዊ ሰልፍ “የጠለምት አማራ ማንነት ጥያቄ የፍትሕ ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጥያቄ ነው” ብለዋል።
ነዋሪዎቹ ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ የተለያዩ መፈክሮችንም አሰምተዋል።
ሕወሓት ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ በኀይል አካባቢውን ወደ ትግራይ አካሎት የቆየ መኾኑን ያነሱት ነዋሪዎቹ በአሁኑ ጊዜ አካባቢው ግፍ ሲፈጽምበት ከነበረው አገዛዝ ላለፉት ሰላሳ ዓመታት በዱር በገደሉ በመታገል ነጻ መውጣቱን አስገንዝበዋል።
የማንነት ጥያቄያቸው ሕጋዊ ኾኖ የአካባቢያቸውን ሰላምና ልማት እንዲያስቀጥሉም መንግሥት ምላሽ እንዲሠጣቸው ጠይቀዋል።
ዘጋቢ፦ ተስፋዬ አይጠገብ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
