
ባሕር ዳር: ሰኔ 09/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ለመጀመሪያ ጊዜ በአዊኛ ቋንቋ የተሠራው “አንታጉ” የተሰኘው ፊልም ለአዊኛ ቋንቋ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ባሕል እና ቱሪዝም መምሪያ ገልጿል፡፡
581 የፊልም ተዋናዮች የተሳተፉበት “አንታጉ” የተሰኘው ፊልም በአዊኛ ቋንቋ የተሠራ ነው። ሰኔ 15/2015 ዓ.ም በአዊ ባሕል አዳራሽ እንደሚመረቅ ተገልጿል፡፡
የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ባሕል እና ቱሪዝም መምሪያ ኀላፊ ለይኩን ሲሳይ እንዳሉት “አንታጉ” የተሰኘው ፊልም ከሕዝብ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ነው የተሠራው፡፡
የባሕል እና ቱሪዝም መምሪያውም ሙያዊ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ለፊልሙ ስኬት የድርሻውን ማበርከቱ ታውቋል፡፡
የፊልሙ መሠራት ለአዊኛ ቋንቋ እድገት አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የመምሪያው ኀላፊ ለአሚኮ ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ፡- አዳሙ ሽባባው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!