የቀጣይ ዓመት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር መርሐ ግብር ይፋ ኾነ

332

ባሕር ዳር: ሰኔ 08/2015 ዓ.ም (አሚኮ) መርሐ ግብሩ እንዳመላከተው የፕሪሚየር ሊጉ የውድድር ሳምንት በነሐሴ 05 ቀን 2015 ዓ.ም ይጀመራል፡፡ የ2023/24 የሊጉ ጨዋታ የመክፈቻው ዕለት የእንግሊዝ እና የአውሮፓ ሻምፒዮኑ ማንቸስተር ሲቲ ከአዲስ አዳጊው በርንሌይ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡ በዚሁ የመጀመሪያ ሳምንት የጨዋታ መርሐ ግብር ላይ ቼልሲ ሊቨርፑልን ይገጥማል፡፡ በተጨማሪም አርሰናል ኖቲንግሃም ፎረስትን እንዲሁም ማንቼስተር ዩናይትድ ወልቭስን በመጀመሪያው ሳምንት የሚጫወቱ ይሆናል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየፈተና ጥሪ ማስታወቂያ
Next articleአምባሳደር ስለሺ በቀለ በአሜሪካ ከሚገኙ ከ36 በላይ የዳያስፖራ አደረጃጀት ኃላፊዎችና ተወካዮች ጋር ተወያዩ።