አየር መንገዱ 6 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አገኘ።

103

ባሕር ዳር: ሰኔ 08/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተያዘው በጀት ዓመት 6 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡ የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሰጡት መግለጫ በተያዘው በጀት ዓመት የኢትዮጵያ አየር መንገድ 13 ነጥብ 7 ሚሊዮን መንገደኞች ማጓጓዙን ተናግረዋል፡፡ በኮቪድ 19 ወቅት ተቋርጠው የነበሩ በረራዎችን ከመመለስ በተጨማሪ ወደ ሰባት አዳዲስ መዳረሻዎች በረራ መጀመሩንም አንስተዋል፡፡

የአውሮፕላን ቁጥርን ለማሳደግ በተሰራው ሥራም 12 አዳዲስ የመንገደኛ አውሮፕላኖችን ወደ ሥራ ማስገባት መቻሉን ነው የገለጹት፡፡ በአየር መንገዱ የጥገና እና ምህንድስና ማዕከል ከመንገደኛ ወደ ጭነት አገልግሎት ሰጪነት የተቀየሩ ሁለት አውሮፕላኖች የካርጎ ሥራ መጀመራቸውንም ጠቁመዋል፡፡ ዘገባው የኤፍ ቢ ሲ ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በበቂ መጠን እና ዓይነት ምርጥ ዘር ቀርቧል” የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ
Next articleየፈተና ጥሪ ማስታወቂያ