
ባሕር ዳር፡ ሕዳር 20/2012ዓ.ም (አብመድ) 10ኛው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ማኅበር በባሕር ዳር ቅርንጫፍ ዓመታዊ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
በውይይቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ማኅበር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደምረው ጌታቸው እየተካሄደ የሚገኘው ውይይት የተለያዩ ሐሳቦች የሚመነጩበት፣ አዳዲስ ለሚወጡ ፖሊሲዎች ግብዓት የሚሆኑበት፣ የነበረው አሰራር የሚገመገምበት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
‹‹የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎረሜሽን ተግዳሮቶች ከአማራ ክልል አንጻር›› በሚል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ንግድ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ በአቶ መላኩ አለበል፣ ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በመምህር ጌታቸው ይርጋ (ዶክተር) እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመምህር ጌትነት ዓለሙ (ዶክተር) የውይይት የመነሻ ሐሳቦች እየቀረቡ ነው፡፡
በመድረኩ የባሕር ዳር እና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ምሁራን፣ የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው፡፡
ዘጋቢ፡- ብሩክ ተሾመ