በወቅታዊ ቀጣናዊ ጂኦ-ፓለቲካ የደኅንነት ሁኔታ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነት ያለው አንድምታ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው።

30

ባሕር ዳር: ሰኔ 08/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በወቅታዊ ቀጣናዊ ጂኦ-ፓለቲካ የደኅንነት ሁኔታ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነት ያለው አንድምታ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

በዝግጅቱ ላይ የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዩ የፖሊሲ አማካሪ አምባሳደር ምንሊክ ዓለሙ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች፤ ምሁራን እና የመከላከያ ሠራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በፓናሉ ላይ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች እና ከመከላከያ ጥናት እና ምርምር ማዕከል በተውጣጡ እና በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው ዲፕሎማቶች፤ ምሁራን እና ወታደራዊ አመራሮች የተዘጋጁ ጥናታዊ ጽሑፎች ለውይይት እንደሚቀርቡ የወጣው መርሐ-ግብር እንደሚያሳይ ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበጦርነት ለተጎዱ ከአራት ሺህ በላይ አርሶአደሮች የምርጥ ዘር ድጋፍ ተደረገላቸው።
Next articleጋዜጠኛ ሕይወት ታደሰ ለልብ ህሙማን መርጃ ማእከል ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ የሚቆጠር ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች።