ለደቡብ ወሎ ዞን የፋይናንስ ተቋማት ከ18 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ የተደረገባቸው የቢሮ መገልገያ ቁሶች ድጋፍ ተደረገ።

83

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 07/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው በደቡብ ወሎ ዞን ለሚገኙ የወረዳና ከተማ አስተዳደሮች የፋይናንስ ተቋማት ከ18 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ የተደረገባቸው የቢሮ መገልገያ ቁሶችን ድጋፍ አድርጓል።

በጦርነቱ የደቡብ ወሎ ዞን ከ91 ቢሊየን ብር በላይ ውድመት አስተናግዷል።

በጦርነቱ ምክንያት የደረሰው ውድመት በመንግስት ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ተጽዕኖም ፈጥሯል። የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው በተዋረድ ለሚገኙ የተለያዩ የመንግስት ተቋማት የቢሮ መገልገያ ቁሶችን ድጋፍ እያደረገ ነው።

ቢሮው ለሶስተኛ ጊዜ በጦርነቱ ለተጎዱ ተቋማትና ወረዳዎች የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ቁሶችን ድጋፍ ማድረጉን የደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ እቴነሽ ጌታቸው ቁሶቹን ለወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ባስረከቡበት ጊዜ አስታውቀዋል።

እየተደረገ ያለው ድጋፍ ውድመቱን የሚሸፍን ባይሆንም ቢሮው አገልግሎት ለመስጠት ወሳኝ ናቸው ብሎ ያመነባቸው የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶችን ከ18 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ በማድረግ ግዥ ፈጽሞ ማስረከቡን አስረድተዋል።
በኢ ስፔስ ፕሮጀክት ለገንዘብ ተቋማቱ ምቹ የሥራ ሁኔታ ለመፍጠር የሚያስችል ድጋፍ ስለመደረጉ ያወሱት ወ/ሮ እቴነሽ ቢሮው ድጋፉን አመቻችቶ በማቅረቡ ምስጋናቸውን ገልጸዋል።

መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትም ጦርነቱ በዞኑ ያደረሰውን ጉዳት በማጤን አስፈላጊ ድጋፎችን በማድረግ እንዲያግዙ ኃላፊዋ ጥሪ ማቅረባቸውን የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ መረጃ ያመላክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አርማ የታተመባቸውን የኪስ ቦርሳዎች በማዘጋጀትና መታወቂያ በማስመሰል ለሕገወጥ ተግባራት ጥቅም ላይ ለማዋል ሙከራ ሲያደርጉ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
Next article“የትምህርት ቤታችንን ክብር የሚመጥን ውጤት ለማስመዝገብ እየተዘጋጀን ነው” ተማሪዎች