“የአማራ ክልል ካሳለፈው ውስብስብ ፖለቲካዊ ፈተና አንጻር ሥልጠናው አስፈላጊ ነው” አቶ እርስቱ ይርዳው

167

ባሕር ዳር: ሰኔ 05/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አቅጣጫዎች ዙሪያ የሥልጠና መድረክ ተጀምሯል። የማዕከላዊ ኮሚቴው ከሰሞኑ በነበረው ውይይት ያስቀመጣቸውን አቅጣጫዎች በሚመለከት ከአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ጋር ለቀጣዮቹ አምስት ቀናት ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል።

የማዕከላዊ ኮሚቴው አመራሮች በሚመሩት የፓርቲው ሥልጠናዊ መድረክ የአማራ ክልል ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮችን ሥልጠና ለማስተባበር የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳድር እርስቱ ይርዳውን ጨምሮ የሌሎች ክልሎች አመራሮች ተገኝተዋል።

“ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በገጠሟት ፈተናዎች ዉስጥ ሆና አበረታች ውጤቶችን አስመዝግባለች ያሉት አቶ እርስቱ የተሻገርንባቸው መንገዶች ብስለት የተሞላበት ነበር” ብለዋል።

ፈተናዎችን ወደ እድል ለመቀየር መነጋገር እና የጋራ አስተሳሰብ መያዝ ያስፈልጋል ያሉት ርእሰ መሥተዳድር እርስቱ ስልጠናው በሁሉም ክልሎች እንደሚካሄድ አንስተዋል።

“የአማራ ክልል ካሳለፈው ውስብስብ ፖለቲካዊ ፈተና አንጻር ሥልጠናው አስፈላጊ ነው” ያሉት አቶ እርስቱ ይርዳው የሚነሱ ሃሳቦች ለሀገር፣ ለመንግሥት እና ለፖርቲ ስለሚጠቅም ዓላማውን ታሳቢ ያደረገ ተሳትፎ ያስፈልጋል ብለዋል።

ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበቻይና በተካሄደ የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 7ኛ ተከታትለው በመግባት አሸነፉ
Next articleከክረምት መግባት ጋር በተያያዘ በተመላሽ ተፈናቃይ ዜጎች አካባቢ ወባና መሰል በሽታዎች እንዳይከሰቱ ክትትል እየተደረገ መኾኑ ተገለጸ፡፡