ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዕውቅና ሰጠ።

103

ባሕር ዳር: ሰኔ 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ለአማራ ሚዲያ ኮርፕሬሽን እውቅና ሰጥቷል። 60ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን ያከበረው ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በዓመታት ጉዞው አስተዋጽኦ ላደረጉለት ተቋማት እና ግለሰቦች ዕውቅና ሰጥቷል። ዩኒቨርሲቲው አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በዓመታት ጉዞዬ አስተዋጽኦ ያደረገልኝ ተቋም ነው ሲል ዕውቅና ሰጥቶታል።

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር መሥራት ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል። አሚኮ በዩኒቨርሲቲው የሚካሄዱ ዝግጅቶችን በዜና እና በፕሮግራሙ በተለያዩ አማራጮች ያደርሳል። ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ እና አሚኮ በመተባበር “መስኮተ ጥበብ” የተሰኘ ሳምንታዊ ዝግጅት ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ ለሕዝብ እያቀረቡ ነው።

መስኮተ ጥበብ ዝግጅት ስለ ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ዝግጅቶች የሚቀርብበት ነው። የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ምሁራን በአሚኮ ምሁራዊ ትንታኔዎች እና መፍትሔ አመላካች ሀሳባችን በመስጠት ትብብር ያደርጋሉ። አማራ ሚደያ ኮርፖሬሽን ለሀገር ሰላም፣ ለሕዝብ አንድነት፣ ልማት፣ ፖለቲካዊ መረጋጋት እና ሌሎች ጉዳዮች በሚሠራው ሥራ በተለያዩ ተቋማት ዕውቅና የተሰጠው ተቋም ነው። አሚኮ ሕዝባዊ ወገንተኝነትን በማስቀደም ከ10 በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቋንቋዎችን በመጠቀም በትጋት እየሠራ የሚገኝ ሚዲያ ነው።

ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞንና ኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር አዋሳኝ አካባቢዎች የሚከሰቱ አለመረጋጋቶችን በመቅረፍ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እየሠራን ነው” የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ
Next articleበአማራ ክልል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኀብረት ሥራ ዩኒየኖች 6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ብድር ማሰራጨታቸው ተገለጸ።