
ባሕር ዳር: ሰኔ 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የቀድሞው የሶቬት ኅብረት የአሁኗ ሩሲያ ለባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ መመሥረትና ዘመናዊ ትምህርት በኢትዮጵያ እንዲስፋፋ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጋለች።
በዘመነ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የቀድሞዋ ሶቬት ኅብረት የአሁኗ ሩሲያ በሀገሪቱ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም እንዲገነባ ከፍተኛ ድጋፍ አድርጋለች።
ዩኒቨርሲቲው ለሩሲያ የሰጠውን እውቅና በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ትርኪሂን ተቀብለዋል።
ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ለ44 ሀገራት ኤምባሲዎች፣ ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽንና ለሌሎች የሚዲያ ተቋማት፣ ለተለያዩ ተቋማት፤ ለቀድሞ ተማሪዎችና መምህራን እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት እውቅና ሰጥቷል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!