“ስልታዊ አጋርነት እና ትብብር ለዘላቂ የዓባይ እና አዋሽ ተፋሰሶች ልማት” በሚል ጭብጥ ያተኮረ 2ኛው ዓለም አቀፍ ጉባዔ በወሎ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።

48

ደሴ : ሰኔ 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በወሎ ዩኒቨርሲቲ የሚመራው የዓባይ አዋሽ ተፋሰሶች የምርምር ተቋም እና በዓለም አቀፍ የውኃ ምርምር ተቋም በጋራ የተዘጋጀው ይህ ጉባዔ ለሁለት ቀናት ይካሄዳል።

በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የወሎ የኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትና የጥናታዊ ምርምር አባላት፣የዓባይና አዋሽ ተፋሰሶች የምርምር ተቋም ዳይሬክተር ወንድዬ አድማሱ (ዶ.ር) ፣ በውጭ ጉዳይ ሚንስተር የድንበር ተሻጋሪ ሃብቶች አማካሪ አምባሳደር ኢብራሂም ኢድሪስን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የዘርፉ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

የኮንፈረንሱ ዋና ዓላማ የዓባይና አዋሽ ተፋሰሶች ለዘላቂ ልማት ስትራቴጂካዊ አጋርነትና ትብብር ሲኾን ከዚህ ጋር በተያያዘም፦

➣የውኃ ፖለቲካና አሥተዳደር

➣የውኃ ሃብትና ክልላዊ ሽርክና

➣የተፈጥሮ ሃብት አሥተዳደር እና

➣የአየር ንብረት ለውጥ ላይ ትኩረት ያደረጉ ጥናታዊ ምርምሮች እንደሚቀርቡ ተገልጿል።

ዘጋቢ:-ሰልሀዲን ሰይድ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርእሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ የሚመራ ልዑክ ባሕር ዳር ገብቷል።
Next article“የዩኒቨርሲቲ እድገትና የሀገር ብልጽግና ተመጋጋቢ ናቸው” አቶ አደም ፋራህ