በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርእሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ የሚመራ ልዑክ ባሕር ዳር ገብቷል።

1492
Made with LogoLicious Add Your Logo App

ባሕር ዳር: ሰኔ 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርእሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ የሚመራ ልዑክ ባሕር ዳር ገብቷል።

ልዑኩ በባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) እና የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኅላፊዎች አቀባበል አድርገውለታል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ርእሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ እና ልዑካቸው በቆይታቸው ከርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) እና ከክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኅላፊዎች ጋር በሁለቱ ክልሎች የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ውጤት ነው” ፍሬው ተገኘ (ዶ.ር)
Next article“ስልታዊ አጋርነት እና ትብብር ለዘላቂ የዓባይ እና አዋሽ ተፋሰሶች ልማት” በሚል ጭብጥ ያተኮረ 2ኛው ዓለም አቀፍ ጉባዔ በወሎ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።