የአማራ እና የአፋር ክልል ሕዝቦችን የጋራ ልማትና ሰላም ለማጠናከር ያለመ ውይይት በደሴ ከተማ እየተካሄደ ነው።

92

ደሴ : ሰኔ 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ሰላም ሚኒስቴር ባዘጋጀው በዚህ መድረክ የሁለቱም ክልሎች የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊዎችን ጨምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በውይይት መድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኀላፊ ኮማንደር መንገሻ አውራሪስ የአማራ እና የአፋር ሕዝቦች ዘመናትን የተሻገረ የአብሮነት ትስስር ያላቸው ሕዝቦች መሆናቸውን ገልጸዋል።

ሁለቱ ክልሎች ያላቸው ባሕላዊ የእርቅ ሥርዓት ለሌሎች አካባቢዎች በአርዓያነት የሚጠቀስ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

በውይይት መድረኩ ከሁለቱም ክልሎች የጸጥታ አመራሮች፣ የተለያዩ የሥራ ኃላፊዎችና የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝምና መንግሥታት ግንኙነት እንዲሁም የግጭት አሥተዳደር መሪ ሥራ አስፈጻሚዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በመድረኩ የውይይት መነሻ ጽሑፍ እየቀረበ ሲሆን የሁለቱን ክልል ሕዝቦች ሰላምና ልማት የበለጠ የሚያስቀጥሉና የሚያረጋግጡ ሃሳቦች እየቀረቡ ነው።

ዘጋቢ፦ አሊ ይመር

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ለ4 የዩኒቨርስቲው ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እድገት ሰጠ።
Next article“ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ውጤት ነው” ፍሬው ተገኘ (ዶ.ር)