ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ለ4 የዩኒቨርስቲው ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እድገት ሰጠ።

82

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ ሰኔ 03/2015 ዓ/ም ባደረገው ስብሰባ ለ4 የዩኒቨርስቲው ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እድገት ሰጥቷል።

በዚሁም መሰረት ፦

1ኛ. ዶ/ር ጌታቸው ዓለማየሁ ዳሞት ከግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ በአግሮኖሚ የሙሉ ፕሮፌሰርነት

2ኛ. ዶ/ር ንጉስ ጋብዬ ሀብቱ ከባሕርዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በኬሚካል ኢንጅነሪንግ ሙሉ ፕሮፊሰርነት

3ኛ. ዶ/ር መላኩ ዋለ ፈረደ ከሳይንስ ኮሌጅ በኢንቶሞሎጂ ሙሉ ፕሮፌሰርነት

4ኛ. ዶ/ር ፀጋዬ ካሳ ጎጂ ከሳይንስ ኮሌጅ በሥነ-ህዋ ሳይንስ ሙሉ ፕሮፌሰርነት እድገት ማግኘታቸውን ዩኒቨርሲቲ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

አንጋፋው ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት 60ኛ ዓመት የብርኢዮቤልዩ በዓሉን በማክበር ላይ ይገኛል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ 60ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን እያከበረ ነው።
Next articleየአማራ እና የአፋር ክልል ሕዝቦችን የጋራ ልማትና ሰላም ለማጠናከር ያለመ ውይይት በደሴ ከተማ እየተካሄደ ነው።