በኢጋድ አባል ሀገራት በቀውስ አያያዝና ግጭቶችን በማስቀረት ረገድ ለውጦች መታየታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር) ገለጹ።

259

በኢጋድ አባል ሀገራት በቀውስ አያያዝና ግጭቶችን በማስቀረት ረገድ ለውጦች መታየታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር) ገለጹ።

የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) አባል ሀገራት ርዕሳነ ብሔራት እና ርዕሳነ መንግሥታት 13ኛውን መደበኛ ስብሰባ አዲስ አበባ ላይ እያካሄዱ ነው።

በስብሰባው መክፈቻ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር) እንደተናገሩት አባል ሀገራቱ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቀውስ አያያዝና ግጭቶችን በማስቀረት ረገድ ለውጦች መታዬታቸውን አመልክተዋል።

አባል ሀገራቱ በቀጣናው ሠላም እንዲሰፍንና ልማት እንዲጠናከር የሚያደርጉትን ጥረትም በስኬትነት ጠቅሰዋል።

አባል ሀገራት ኢትዮጵያ ተቋሙን ለበርካታ ዓመታት እንድትመራ አመኔታ ማሳደራቸውንም ዶክተር ዐብይ አድንቀዋል።

ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

Previous articleያለኢንዱስትሪ ግንባታ የከተሞች መስፋፋት የኑሮ ውድነቱን እና ሥራ አጥነትን ከማባባስ ያለፈ ፋይዳ እንደማይኖረው የወልድያ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡
Next articleየባቡር ፕሮጀክቱን የሀገሪቱ ኪሳራ ከመሆን በመታደግ የኢኮኖሚ ማሳለጫ እንዲሆን የፉክክር ምዕራፎችን መዝጋት እንደሚያስፈልግ የአዋሽ-ወልድያ-ሀራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት አስታወቀ።