ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ 60ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን እያከበረ ነው።

58

ባሕር ዳር: ሰኔ 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ 60ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል የማጠቃለያ ዝግጅት እየተካሄደ ነው።

“ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ” እያለ ዓመታትን የተሻገረው አንጋፋው ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ 60ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን እያከበረ ይገኛል።

ጥበብ፣ ስልጣኔ፣ ታላቅነት፣ ቀደምትነት እና ሩቅ ተጓዥነት ከሚቀዳበት፣ ለዘመናት እየተቀዳ ትውልድ ከጠጣበት፣ ጠጥቶም ከረካበት ከግዮን ጓዳ፣ የከበረ ታሪክ ከመላበት፣ ምስጢር ከበዛበት፣ ቅዱሳን ከሚኖሩበት፣ ገዳማት ከተገደሙበት፣ ከምሥጢራዊ ከጣና ሐይቅ ዳር ተመሥርቶ ጥበብን ከፍልቀቱ ሲቀዳ ኖሯል።

ለዓመታት ጥበብ እየቀዳ ሀገር የኮራችባቸውን፣ እንኳን ወለድኳቸው፣ እንኳንም አስተማርኳቸው ያለቻቸውን ተማሪዎችን፣ ትውልድ ያነፁ መምህራንን ሲያፈራ ኖሯል።

ከበዓይ ጓዳ ጥበብን እየቀዳ ለተጠሙት እያጠጣቸው፣ አጠጥቶም እያረካቸው ኖሯል። ዛሬም ጥበብን ለተጠሙ ከግዮን እየቀዳ፣ ከጣና እየጨለፈ እያጠጣቸው ይገኛል። ይህ ከግዮን ጓዳ ጥበብ የሚቀዳበት የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲም 60ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን የማጠቃለያ ዝግጅት እያከበረ ነው።

ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበሀገሪቱ የሕግ የበላይነት ማስፈን የመንግስት ተቀዳሚ ተግባር ነው ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልገሎት አስታወቀ፡፡
Next articleባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ለ4 የዩኒቨርስቲው ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እድገት ሰጠ።