
አዲስ አበባ፡ ሰኔ 03/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የመንግሰት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሰ ቱሉ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
በሀገሪቱ የሕግ የበላይነትን ማስከበር የመንግስት ተቀዳሚ ተግባር ነው ያሉት ዶክተር ለገሰ፤ አንድ ጠንካራ የመከላከያ እና የፌዴራል ፖሊስ የመገንባት ሒደቱ እየቀጠለ ነው ብለዋል፡፡
በሀገሪቱ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን ለማጎልበት እና ኢትዮጵያን “አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት” ለማድረግ ሰላም ለማስፈን በቤንኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተደረገው የሰላም ሒደት ውጤት ማምጣቱን ገልጸዋል፡፡ ከሸኔ ጋር የሚደረገው የድርድር ሒደትም ይቀጥላል ብለዋል።
ዶክተር ለገሰ እንዳሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ.ር) ሰሞኑን ከመንግስት ከፍተኛ አመራሮች እና የክልል የሥራ ኃላፊዎች ጋር ያደረጉት ግምገማ የበጀት ዓመቱ የ9 ወር እቅድ እና ትግበራ፣ ሁለተኛው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ እና ሀገራዊ ዲፕሎማሲያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ናቸው ብሏል። በጉዳዮቹ ላይ ለአመራሮቹ ተመሳሳይ ግንዛቤ መፍጠር መቻሉን ተናግረዋል፡፡
በታክስ ፖሊሲ አሥተዳደር አካሄድ ላይ የተሠሩት ማሻሻያዎች እና አካሔድ ላይ 9 ነጥብ 3 በመቶ እድገት ማምጣት ተችሏል ብለዋል ዶክተር ለገስ።
አካሔዱ አዲስ የታሪክ እጥፋት ላይ መኾናችንን የሚያሳይ ነው። ይህም ከነጠላ አካሔድ ወደብዝሀ ኢኮኖሚ እና አቅጣጫ ላይ መድረሱ ነውም ብለዋል።
ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማእድን እና ቱሪዝም ዲጅታል ኢኮኖሚን ማዳበር ላይ ትኩረት ድርጓል ተብሏል።
ኢኮኖሚው ከስብራት ተነስቶ በ2023 ወደ 158 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር ለመሻገር ስለሚፈልግ ማክሮ ኢኮኖሚው በተለያየ መንገድ የተሻለ ሪፎርም ላይ ትኩረት አድርጎ የተሠራ መኾኑንም በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡
የበጋ ግብርና ላይ የታየው ውጤት በክረምት እርሻ በድጋሜ በአግባቡ መሠራት ይኖርበታል ብለዋል። የትኛውም የእርሻ መሬት ጾሙን ማደር የለበትም ብለዋል።
በክረምት ወቅት የሚያጋጥሙ ጎርፍ እና ወባ ወረርሽኝ ራሱን እየጠበቀ የአረንጓዴ ዐሻራውን በአግባቡ አስቀምጧል ብለዋል።
ሰሞኑን ከእርዳታ መቋረጥ እና ያለአግባብ መጠቀም ጋር በተያያዘ በመንግስት ላይ የቀረበው የክስ ሃሳብ ፖለቲካዊ ዓላማ ያለው እና ፕሮፖጋንዳ ነውም ብሎታል። የችግሩን መጠን በመለየት ድጋፉ በተለየ መንገድ ያለአግባብ የሚጠቀሙ ካሉ ተለይቶ ርምጃ ይወሰድባቸዋልም ብለዋል። ጉዳዩን የሚመረምር ኮሚቴ መቋቋሙንም ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ካለበት ስብራት ተላቆ በ2023 ወደ 158 ቢሊየን ዶላር ሀገራዊ ምርት ማስመዝገብ የሚችልበት እቅድ ተነድፏል ተብሏል፡፡
ሰሞኑን ከእርዳታ መቋረጥ እና ያለአግባብ መጠቀም ጋር በተያያዘ በመንግስት ላይ የቀረበው የክስ ሃሳብ ፖለቲካዊ ዓላማ ያለው እና ፕሮፖጋንዳ ነውም ብለውታል ዶክተር ለገሰ።
ዘጋቢ፡- አንዱዓለም መናን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!