“ለከተማችሁ ሕዝብ ክብርና ለማለያ ፍቅር ብላችሁ የገጠማችሁን ፈተና ሁሉ እየተጋፈጣችሁ አሁን ከደረሳችሁበት ወሳኝ ምዕራፍ ደርሳችኋል።” ድረስ ሳኅሉ (ዶ.ር)

118

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 03/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሳኅሉ (ዶ.ር) ለባሕር ዳር ከነማ እግር ኳስ ቡድን ያስተላለፉት የመልካም ምኞት መልእክት አስተላልፈዋል።

“ውድ የባሕር ዳር ከነማ ተጫዋቾች እና ዕንቁ ደጋፊዎች የክለቡ አመራሮች ክቡር አሰልጣኛችን ደግአረገ ለከተማችሁ ሕዝብ ክብርና ለማለያ ፍቅር ብላችሁ የገጠማችሁን ፈተና ሁሉ እየተጋፈጣችሁ አሁን ከደረሳችሁበት ወሳኝ ምዕራፍ ደርሳችኋል።

በተለይ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ጋር የሚኖራችሁ ግጥሚያ እጅግ ወሳኝና ለዘመናት ዋንጫ ማንሳት የናፈቀውን ድንቅ ደጋፊያችሁን አንጀት የምታርሱበት ነውና በፍፁም መረጋጋት እና ልበሙሉነት ተረጋግታችሁ እንድትጫወቱ የመሪነት እና ወንድማዊ ምክሬን እየለገስሁ መልካም እና የድል ጨዋታ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ ። በጨዋታው ብገኝ እጅግ ደስ ባለኝ ነበር ።

ነገር ግን እኔ በሌላ ሥራ ምክንያት ባልገኝም ባልደረቦቼ በጨዋታው ስለሚታደሙ ቅር እንደማትሰኙ ተስፋ አለኝ። መልካም ጨዋታ ይሁንልን ።” ብለዋል ዶክተር ድረስ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleአትሌት ለሜቻ ግርማ የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል የዓለም ክብረ ወሰን ሰበረ።
Next articleበጉጉት ሲጠበቅ የቆየው የባሕር ዳር ከነማ እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ጨዋታ ዛሬ ይካሔዳል።