
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 03/2015 ዓ.ም (አሚኮ) አትሌት ለሜቻ ግርማ ትላንት ምሽት በፓሪስ በተካሄደዉ ዳይመንድ ሊግ ውድድር የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ሩጫ ውድድር የዓለም ክብረወሰን በመስበር አሸንፏል።
7:52.11 በሆነ ደቂቃ የገባው ለሜቻ ግርማ በሳይፍ ሳኢድ ተይዞ የነበረውን ሪከርድ ከአስራ ስምንት ዓመታት በኋላ የግሉ ማድረጉን ከዓለም አትሌቲክስ ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ሌላኛው በርቀቱ የተካፈለው ኢትዮጵያዊው አትሌት አብርሀም ስሜ 8:10.73 በሆነ ደቂቃ አራተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!